ክርስትና
ተመለስ

Psalms 143

የማሽን ትርጉም፡ እስካሁን ወደ ቋንቋህ ምንም የታተመ የዚህ መጽሐፍ ትርጉም የለም።

1አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህም ልመናዬን አድምጥ፤ በጽድቅህም መልስልኝ።

2ከአገልጋይህም ጋር ወደ ፍርድ አትግባ፥ ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና።

3ጠላት ነፍሴን አሳድዷልና፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ አደቀቃት፤ ከብዙ ዘመን በፊት እንደ ሞቱ በጨለማ አኖረኝ።

4መንፈሴም በውስጤ ደከመብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።

5የቀደመውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ አወጣሁ አወረድሁ።

6እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴ እንደ ደረቅ ምድር አንተን ተጠማች። ሴላ።

7አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ አልቋልና፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልሆን፥ ፊትህን ከእኔ አትሰውር።

8በአንተ ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።

9አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።

10አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን እንዳደርግ አስተምረኝ፤ መልካሙ መንፈስህ በቅን ምድር ይምራኝ።

11አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራ አውጣት።

12በምሕረትህም ጠላቶቼን ቍረጣቸው፤ እኔ አገልጋይህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቋትን ሁሉ አጥፋቸው።

ምንጭ: Berean Standard Bible

WEBREATH · 11:11

«He himself gives everyone life and breath and everything else» — Acts 17:25

Breath is one for all: everyone lives by it, whoever they are and whatever they believe. Every day at 11:11 local time people stop for sixty seconds, breathe, and thank GOD for the breath — each in their own words, each within themselves. In that minute we are One Breath.

WEBREATH — the Minute at 11:11, your own local time — we are One Breath