1 Thessalonians 5
የማሽን ትርጉም፡ እስካሁን ወደ ቋንቋህ ምንም የታተመ የዚህ መጽሐፍ ትርጉም የለም።
1ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤
2የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና።
3ሰዎች፦ «ሰላምና ደኅንነት ነው» በሚሉበት ጊዜ፥ ምጥ እርጉዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፥ ከቶም አያመልጡም።
4እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፤
5ሁላችሁ የብርሃን ልጆችና የቀን ልጆች ናችሁና፤ እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም።
6እንግዲያስ እንደ ሌሎች አንተኛ፥ ነገር ግን ነቅተን በመጠን እንኑር።
7የሚተኙ በሌሊት ይተኛሉና፥ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና።
8እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ የራስ ቍር አድርገን በመጠን እንኑር፤
9እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።
10የነቃንም ብንሆን ያንቀላፋንም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።
11ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉት፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፥ አንዱም አንዱን ያንጽ።
12ወንድሞች ሆይ፥ በመካከላችሁ በትጋት የሚሠሩትን፥ በጌታ የሚገዟችሁንና የሚያሳስቧችሁንም እንድታውቋቸው እንለምናችኋለን፤
13ስለ ሥራቸውም በፍቅር እጅግ አክብሯቸው። እርስ በርሳችሁ በሰላም ኑሩ።
14ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጿቸው፥ ፍርሃት ያደረባቸውን አጽኗቸው፥ ደካሞችን እርዱ፥ ሰውንም ሁሉ ታገሡ።
15ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።
16ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
17ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
18በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።
19መንፈስን አታጥፉ፤
20ትንቢትን አትንቁ፤
21ሁሉን ፈትኑ፥ መልካሙንም ያዙ፤
22ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።
23የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።
24የሚጠራችሁ የታመነ ነው፥ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።
25ወንድሞች ሆይ፥ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።
26ከወንድሞች ሁሉ ጋር በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።
27ይህ መልእክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አምላችኋለሁ።
28የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
WEBREATH · 11:11
«He himself gives everyone life and breath and everything else» — Acts 17:25
Breath is one for all: everyone lives by it, whoever they are and whatever they believe. Every day at 11:11 local time people stop for sixty seconds, breathe, and thank GOD for the breath — each in their own words, each within themselves. In that minute we are One Breath.
WEBREATH — the Minute at 11:11, your own local time — we are One Breath